የመላእክት መዝሙራት

ይበራል በክንፉ

ይበራል በክንፉ

ይበራል በክንፉ ምልጃው ፈጣን ነው

የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው

ያሳደገኝ መላክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው /2// /2/

 

ከፊቴ ቀደመ ደመናውን ዘርግቶ

እንዳልደናቀፍ ጉድጓዶችን ሞልቶ

ዛሬ ላለሁበት ብርቱ ጉልበት ሆነኝ

ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ

 

አዝ…

 

በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ

አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ

የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከእርሱ ጋራ

ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ

 

አዝ…

 

በዙሪያዬ ተክሎች የሳት ምሶሶውን

ፅድቅ እየመገበ አሳደገኝ ልጁን

የአምላኬን ምስጋና ዘወትር እያስጠናኝ

እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ

 

አዝ…

 

ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር

ይሰማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር

ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ

ታላቁን በረከት በውስጤ አፈሰሰ

 

አዝ…

 

ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ

መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ

የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ

በፀጋወ ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ

 

አዝ…

ገብርኤል ነው

ገብርኤል አምለክ የሾመዉ

ገብርኤል ነው አምለክ የሾመዉ [2]

አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነዉ

 

ናቡከደነጾር አንተን በግልፅ አይቶ

ለእግዚአብሄር ሰገደ ያንተን ምስል ትቶ

ሐሰቴን እንደሆነ ይመስክሩ ሶስቱ

ከዚያች ከባቢሎን [2] የወጡት ከእሳቱ

አዝ..

 

ከዓለመ መላእክት ከቅዱሱ ቦታ

የሰዉን ልጅ መረጥህ ልትረዳ ጧት ማታ

እንደ ጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ

ትመስክር ስለአንተ [2] ከነ ልጇ ትምጣ

 

አዝ..

 

ልመስክር ስለአንተ ነህ እና ህይወቴ

ገብርኤል [2] ሰመረ ስእለቴ

የአናብስትን አፍ የዘጋኸዉ መልአክ

ገብርኤል አንተ ነህ [2] በእኛ ሁሉ የታመንክ

 

አዝ..