መልአከ ገነት መምህር አብርሃም ሙጭዬ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ክርስቲያን የተባሉ ምእመናን በኅብረት የሚጠሩበት በመጽሐፍ ቅዱስ ጎልቶ የሚታይ የምእመናን ስያሜ ነው። ማቴ 16፥18 ሐዋ 5፥11፤ 20፥28 ኤፌ 5፥23-33።
ሥርዓተ አምልኮ የተጀመረው እግዚአብሔር ፍጥረቱን እመ ኁበ አልቦ ኁበ ቦ አምጥቶ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። መላእክት ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ”ቅዱስ፣ቅዱስ፣ቅዱስ” እያሉ ፈጣሪያቸውን በማመስገን አምልኮአቸውን የሚገልጹ ስለሆነ አምልኮተ እግዚአብሔር በዓለመ መላእክት ተጀመረ ማለት ነው /ኩፋ 2፥6 8።
ሰውም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለፈጣሪው ይገዛ ነበር። ልጆችም ከአባታቸው ባገኙት መንፈሳዊ ጥበብ መሠረት የአምልኮአቸው መገለጫ የሆነ መሥዋዕት የወንጌል አምሳልና መርገፍ በሆነችው ኦሪት አቅርበዋል።አማናዊት ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው ግንቦት 18 ቀን 33 ዓ.ም እንደሆነ ተጽፏል።
በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው አንዲት፣ቅድስት፣ኩላዊት፣ሐዋርያዊት ቤ/ያናችን በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ማለትም በአፍሪካ በአሜሪካ፣በካናዳ፣ኢንግላንድን ጨምሮ በመላው አውሮፓ፣ በእስያ ና በኢየሩሳሌም የምትታወቅ እና ተቀባይነት ያላት ሲሆን ፤ በዚህ በውጭው ዓለም ለሚገኘው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ እና ለሌላውም ፣ማኅበረሰብ በስደት ምክንያት ባህሉ ን፣ታሪኲንና ማንነቱን እንዳይረሳ ፣ከሃይማኖቱ እንዳወጣ ለማድለግ ፦ ጳጳሳትን ፣ካህናትን ፣ዲያቆናትን ና መምህራንን ልካ ፦ ሃይማኖታዊ፣ማኅበራዊ፣መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች።
በዚሁ መሠርት በኖርዌይ ስታቫንገር የኢ/ኦ/ተ/ ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ታላቁ አባት ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክንን በዓለም መድረክ ወክለው ከላይ ለተገለጸዉ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ወደ ኖርዌይ ስታቫንገር መምጣታቸውን ተከትሎ እ. ኤ. አ 1994 ዓ.ም በፈቃደ እግዚአብሔር ልትመሠረት ችላለች ።
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክንን ታላቅነትና ማንነት በዓለም ያሳወቁ የቤ/ክ ልዩ መልዕክተኛ ነበሩ። ብጹዕ አባታችን ከአምስት በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች ተሰጥኦና ልዩ ልዩ የንግግር ጸጋ፣ ሰብኮ የማሳመንና ተናግሮ የማሳሰብ ሃብት ስለነበራቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤዎች የኢትዮጵያን ቤ/ክ ወክለው እንዲገኙ በወሰነው መሰረት፦ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተካሄዱ ስብሰባዎች ለይ ተገኝተዋል።በዚህም መሠረት በአውሮፓ በነበራቸው አገልግሎት በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ ይኖሩ ከነበሩት በጣት ከሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ምእመናን መካከል ወ/ሮ ኂሩት ከበደ እና ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው አስተምረው፣ መክረውና አባታዊ ቡራኬ ከሰጧቸው በኃላ ቤተክርስቲያን እንዲመሠርቱ በሰጧቸው አባታዊ ማሳሰቢያ መሠረት ምእመናኑን በማሰባሰብ አገልግሎት በ20.07.1994 ዓ.ም (እ. ኤ. አ) ተጀመረ።
በ06.04.2005 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ቤተክርስቲኗ በኖርዌይ ሀገር ሕጋዊ ሆና ተመዘገበች።በአሁኑ ሰዓት የምእመናን ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለማነጽ ወይም ለመግዛት ምእመናን በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።
እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ አባታችን ናቸው።
Kondolanse fra Den Etiopisk Ortodokse Tewahedo Medhanealem kirke i Stavanger
I troen på oppstandelsen og med dyp kristen ærbødighet har vi mottatt budskapet om at Hans Majestet Kong Harald V har fullført sitt jordiske løp og er gått bort. Kongen tjente Norge og det norske folk med stor trofasthet, visdom og hjertevarme gjennom et langt livsverk. Hans uselviske innsats, rettferdighet og kjærlighet til landet vil […]
ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውስተ ገነት፤ ወኩሉ ፍጥረት አሳት ወአናብርት፤ እለ ውስተ ደይን ያእርፉ ባቲ፤ እስመ ባቲ ኣእረፈ እምኩሉ ግብሩ
እንኳን አደረሳችሁ!
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰቷን፣
እንኳን አደረሳችሁ!
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን እና ዕርገቷን ምክንያት በማድረግ የኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ሥርዓተ ቅዳሴና ጉባኤ።
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንፀተ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል እና ለዘመነ አስተምህሮ በሰላም አደረሳችሁ።
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንፀተ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል እና ለዘመነ አስተምህሮ በሰላም አደረሳችሁ።
“ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።” መዝ ፵፮፥፭
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን…በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን…አግዓዞ ለአዳም
ሰላም… እምይእዜሰ
ኮነ…ፍሥሓ ወሰላም
የእሑድ ግንቦት ፪ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (May 10/2026)
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን…በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!!!
“ወበቁስለ ዚአሁ ሐየውነ” «በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን» ትን. ኢሳ. 53÷5
እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ (ለመጋቢት መድኃኔ ዓለም) ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሆሣዕና አደረሳችሁ!
“ወበቁስለ ዚአሁ ሐየውነ” «በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን» ትን. ኢሳ. 53÷5
እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ (ለመጋቢት መድኃኔ ዓለም) ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሆሣዕና አደረሳችሁ!
እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ!
የአይሁድ አለቃ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃለ ምልልስ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ «ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ» ዮሐ. ፫፥፮ ጌታችን ኒቆዲሞስን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው ሲሆን ሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን ቢፈራም ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ […]