• ”እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ” መዝ 135፤ 1

  • ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • "ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም" ምሳ 22፤6

የደብሩ አስተዳዳሪ የ2013 ዓ.ም. የአዲስ አመት መልእክት አስተላለፉ

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ፳፻፲፪ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ፳፻፲፫ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ ! አዲሱን ዓመት የንሥሓ ፣የፍሥሓ የበረከትና የምህረት ፣ የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን ! ከተዋሕዶ ማማ ፣ ከመስቅል ዓላማ ፣ከወንጌል ከተማ ሳያናውጽ በቤቱ በሃይማኖት በምግባር አጽንቶ ያኑረን!! ስለ ሀገራችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ህዝበ እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበት የምናይበት ዘመን ያድርግልን::ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር አይለየን አሜን ።የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ አድሮ ፀንቶ ይኑር::

የደብሩ ድረገጽ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ ቀረበ

ለብዙ አመታት በስራ ላይ ውሎ የነበረው የስታቫንገር የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ድረገጽ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ የቀረበ ሲሆን በድረገጹ መሰረታዊ መረጃዎች፤ወቅታዊ መረጃዎች እንዲሁም ከቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ እና ከደብሩ እንቅስቃሴዎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ መረጃዎች ተካተውበታል።

አገልጋዮች

  • 2003 - 2006

    ቆሞስ አባ ኃይለማርያም (አቡነ አረጋዊ)

  • 2009 - 2018

    መጋቤ ምስጢር ቆሞስ አባ ቴዎድሮስ አካሉ

  • ከ 2018 ጀምሮ

    መልአከ ሰላም ቀሲስ ሙሉጌታ

የቤተክርስቲያኑ አመሰራረት ታሪክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ክርስቲያን የተባሉ ምእመናን በኅብረት የሚጠሩበት በመጽሐፍ ቅዱስ ጎልቶ የሚታይ የምእመናን ስያሜ ነው። ማቴ 16፥18  ሐዋ 5፥11፤ 20፥28 ኤፌ 5፥23-33።

ሥርዓተ አምልኮ የተጀመረው እግዚአብሔር ፍጥረቱን እመ ኁበ አልቦ ኁበ ቦ አምጥቶ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። መላእክት ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ”ቅዱስ፣ቅዱስ፣ቅዱስ” እያሉ ፈጣሪያቸውን በማመስገን አምልኮአቸውን የሚገልጹ ስለሆነ አምልኮተ እግዚአብሔር በዓለመ መላእክት ተጀመረ ማለት ነው /ኩፋ 2፥6 8።

ሰውም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ለፈጣሪው ይገዛ ነበር። ልጆችም ከአባታቸው ባገኙት መንፈሳዊ ጥበብ መሠረት የአምልኮአቸው መገለጫ የሆነ መሥዋዕት የወንጌል አምሳልና መርገፍ በሆነችው ኦሪት አቅርበዋል።አማናዊት ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው ግንቦት 18 ቀን 33 ዓ.ም እንደሆነ ተጽፏል።

በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው አንዲት፣ቅድስት፣ኩላዊት፣ሐዋርያዊት ቤ/ያናችን  በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ማለትም በአፍሪካ በአሜሪካ፣በካናዳ፣ኢንግላንድን ጨምሮ በመላው አውሮፓ፣ በእስያ ና በኢየሩሳሌም  የምትታወቅ እና ተቀባይነት ያላት ሲሆን ፤ በዚህ በውጭው ዓለም ለሚገኘው ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ እና ለሌላውም ፣ማኅበረሰብ  በስደት ምክንያት ባህሉ ን፣ታሪኲንና ማንነቱን እንዳይረሳ ፣ከሃይማኖቱ እንዳወጣ ለማድለግ ፦ ጳጳሳትን ፣ካህናትን ፣ዲያቆናትን ና መምህራንን ልካ ፦ ሃይማኖታዊ፣ማኅበራዊ፣መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ሐዋርያዊ  ተልዕኮዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች።

በዚሁ መሠርት በኖርዌይ ስታቫንገር  የኢ/ኦ/ተ/  ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ታላቁ አባት ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክንን በዓለም መድረክ ወክለው ከላይ ለተገለጸዉ  ሐዋርያዊ  አገልግሎታቸው ወደ ኖርዌይ ስታቫንገር መምጣታቸውን ተከትሎ እ. ኤ. አ 1994 ዓ.ም በፈቃደ እግዚአብሔር  ልትመሠረት ችላለች ።

ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክንን  ታላቅነትና ማንነት በዓለም ያሳወቁ የቤ/ክ ልዩ መልዕክተኛ ነበሩ። ብጹዕ አባታችን ከአምስት በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች ተሰጥኦና ልዩ ልዩ የንግግር ጸጋ፣ ሰብኮ የማሳመንና ተናግሮ የማሳሰብ ሃብት ስለነበራቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤዎች የኢትዮጵያን ቤ/ክ ወክለው እንዲገኙ በወሰነው መሰረት፦ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተካሄዱ ስብሰባዎች ለይ ተገኝተዋል።በዚህም መሠረት በአውሮፓ በነበራቸው አገልግሎት በኖርዌይ ስታቫንገር  ከተማ ይኖሩ ከነበሩት በጣት ከሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ምእመናን መካከል ወ/ሮ ኂሩት ከበደ እና ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው አስተምረው፣ መክረውና አባታዊ ቡራኬ ከሰጧቸው በኃላ ቤተክርስቲያን እንዲመሠርቱ በሰጧቸው አባታዊ ማሳሰቢያ መሠረት ምእመናኑን በማሰባሰብ አገልግሎት  በ20.07.1994 ዓ.ም (እ. ኤ. አ) ተጀመረ።
በ06.04.2005 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ቤተክርስቲኗ በኖርዌይ ሀገር ሕጋዊ ሆና ተመዘገበች።በአሁኑ ሰዓት የምእመናን ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ለማነጽ ወይም ለመግዛት ምእመናን በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።

አድራሻችን

  • +47 458 50 622
  • Tjensvoll Kapell, Henrik Ibsen gata 25, 4021 Stavanger
  • Postboks 113 Sentrum 4001 Stavanger, Norway

መልዕክትዎትን ያጋሩን

© የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ | Webmail | Parish Portal
Website by atbiya.com