ስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
    • ታሪክ
    • አገልጋዮች
  • አገልግሎቶች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • የመድኃኔአለም መዝሙራት
    • የእመቤታችን መዝሙራት
    • የመላእክት መዝሙራት
    • ሁሉም መዝሙራት
  • ይለግሱ
  • የፎቶ ማኅደር
  • ያግኙን
  • Menu Menu

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
​”አነ እፈቅድ እምኀቤከ እጠመቅ ወአንተኑ ትመጽእ ኀቤየ”
(እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል እንጅ አንተ ወደእኔ ትመጣለህ? ማቴ. 3፥14)
​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
​       በመላው ዓለም፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በኖርዲክና ካሪክ ሀገረ ስብከት፣ በኖርዌይ እንዲሁም በስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም አብቢያ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ፦ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶችና ሕፃናት እንኳን
​ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል (ለብርሃነ ጥምቀቱ) በሰላም አደረሳችሁ!
​        መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በማኅፀን እያለ ለጌታው የሰገደና ያመሰገነ ታላቅ ነቢይ ነው። ጌታችን በአካል መጥቶ “አጥምቀኝ” ባለው ጊዜ በታላቅ ትሕትና እና ድንጋጤ ሆኖ ምስክርነቱን ሰጥቷል። በዚህ ታላቅ ዕለት የተከናወኑልን ዐበይት ተግባራት፦
• ​የምሥጢረ ሥላሴ መገለጥ፡ የአንድነትና የሦስትነት ምስጢር የታወቀበት።
• ​የአብ ምስክርነት፡ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” የሚል መመሪያ የተቀበልንበት።
• የጌታ ትሕትና፡ የሰው ልጆች ሁሉ ልዕልና የታየበት።
• ​የውኃ መቀደስ፡ በዮርዳኖስ ተጠምቆ ውኃውን ሁሉ የቀደሰበት።
• ​የዕዳ ደብዳቤ መደምሰስ፡ ዲያብሎስ የቀበረው የዕዳ ደብዳቤ የተደመሰሰበት።
• የትንቢት መፈጸም: የነቢያት ትንቢት የተፈጸመበት
​ስለዚህ ሁላችንም የተደረገልንን ቸርነት በማሰብ፤
• ​እንደ ቅዱስ ዮሐንስ በትሕትና
• ​እንደ ቅዱሳን መላእክት በምስጋና
ጌታ በተጠመቀበት በዮርዳኖስ አምሳል በሆነው የታቦታቱ ማደሪያ (ጥምቀተ ባሕር) ተገኝተን በዓሉን በጋራ እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
​”ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን” (፪ቆሮ. ፱፥፲፭)
​የቅዱሳን አምላክ፣ የአብ የባሕርይ ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይጎብኘን! እንደ ዛሬው ለዛሬ ዓመት በሰላም ያድርሰን!
​         መልካም በዓል!
​መልአከ ገነት መምህር አብርሃም ሙጭየ
የስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
​አውሮፓ፣ ኖርዌይ
ጥር ፳፻፲፰ ዓ.ም (January 2026)

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/photo_2026-01-17_09-07-07.jpg 900 591 Nigussie Girma https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/eotc-stavanger-logo2.png Nigussie Girma2026-01-17 08:14:252026-01-17 08:21:55እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
Search Search

Recent Posts

  • የእሑድ ግንቦት ፪ ቀን  ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (May 10/2026)
  • እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!!!
  • እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ (ለመጋቢት መድኃኔ ዓለም) ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሆሣዕና አደረሳችሁ!
  • እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ!
  • እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • November 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • November 2024
  • June 2021
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • August 2014
  • August 2012
© የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ | Administration | Email | Members Portal
Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: የ2018 ዓ/ም የእንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቸሁ መልእክት፣ ከመምህር አብርሃም ሙጭየ Link to: የ2018 ዓ/ም የእንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቸሁ መልእክት፣ ከመምህር አብርሃም ሙጭየ የ2018 ዓ/ም የእንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ... Link to: የ፳፻፲፰ በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ ክርስትያንሳንድ Link to: የ፳፻፲፰ በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ ክርስትያንሳንድ የ፳፻፲፰ በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ ክርስ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top