እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንፀተ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል እና ለዘመነ አስተምህሮ በሰላም አደረሳችሁ።

👉በዓሉ ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ሲሆን ሕንፀተ ቤተክርስቲያን ይባላል።
የመጀመሪያዋ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ቤተክርስቲያን የታነጸችው ሰኔ 20 ቀን ሲሆን አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጵስዩስ ነው።
ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኗን የቀደሰበትና ያከበረበት ዕለት ነው።
ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 24 ድረስ ያለው ዘመን ዘመነ አስተምህሮ ይባላል።
ዘመነ አስተምህሮ ማለት የጌታችን መውረድ ፣ መወለድ ፣ ዙሮ ማስተማር ፣ መሞት መነሣትና ማረግ እንዲሁም የሐዋርያት ዓለምን ዙሮ ማስተማር የሚነገርበት ዘመን(ጊዜ) ማለት ነው።
የጌታችን ቸርነት!
የእመቤታችን ምልጃ አይለየን!
የሐዋርያት በረከትአይለየን
እሑድ ሰኔ ፳፩/፳፻፲፰ ዓ.ም(21/2018)/(June 28/2026)
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ስታቫንጋር ኖርዌይ!