እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ!

የአይሁድ አለቃ፣ የእስራኤል መምህር ኒቆዲሞስ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃለ ምልልስ ካስተማራቸው ጥቂት ዕድለኛ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ «ከውኃና ከመንፈስ ዳግመኛ ስለ መወለድ» ዮሐ. ፫፥፮ ጌታችን ኒቆዲሞስን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረው ሲሆን ሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን ቢፈራም ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበርም በቅቷል፡፡ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
የኒቆዲሞስ ዕለተ እሑድ መጋቢት ፳ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (March 29/2026) ከደረሱት የስብሐተ ነግህ፣ የኪዳን፣ የቅዳሴ፣ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በጥቂቱ፦
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት
የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን

ስታቫንጋር ኖርዌይ

እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

“እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፤ ወአምላክነሂ ኢያረምም፤ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡” እግዚአብሐር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳቱ በፊቱ ይቃጠላል፡፡ መዝ.፵፱፥፪-፫
እንኳን ለዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት (ደብረ ዘይት) በሰላም አደረሳችሁ!
“ደብረ ዘይት” ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ በደብረ ዘይት ላይ የዓለም ፍጻሜ ምን እንደሚመስል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል፡፡ “እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክትስ ምንድን ነው“? አሉት /ማቴ ፳፬፥፫/ የዓለም ኅልፈት መቼ እንደሆነና ምልክቱ ምን እንደሆነ ለተጠየቀው ጥያቄ ጌታችን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የዓለም ኅልፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ የምትታወቅ እንጂ ቀኒቱ ለሰው ልጅ ተለይታ የማትታወቅ መሆኗን ተናግሯል፡፡ በዓለ ደብረ ዘይት ቤተክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፣ እነዚኽም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ጌና፣ ግዝረት፣ ልደተ ስምዖን፣ ቃና ዘገሊላ፣ ደብረ ዘይትና መስቀል ናቸው፡፡
የደብረ ዘይት ዕለተ እሑድ መጋቢት ፮ ( 6 ) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (March 15/2026) ከደረሱት የስብሐት ነግህ፣ የኪዳን፣ የቅዳሴ፣ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በጥቂቱ፦

እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኖርዌይ የስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአገ ገነት መምህር የኔታ አብርሃም ሙጭየ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

“ድልዋኒክሙ ንበሩ” (ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ማቴ.24÷44)

እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

 

እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ለምኵራብ) በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ለምኵራብ) በሰላም አደረሳችሁ!
“ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ”(“ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላላች” ማቴ.21÷13)
ምኵራብ ማለት:- የአይሁድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ ቤተ መቅደስ ፣ ኮረፍታ ማለት ነው
በዚህ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቤተ መቅደሱን ክብር የገለጠበት በአንጻሩ ለቤተ መቅደሱ ክብር ሳይሰጡ በቤተ መቅደሱ የማይገባ ስራ የሚሰሩትን የገሠጸበትና ያስተማረበት ነው።
ቤተ መቅደስ የተባለው የኢያንዳንዳችን ልብ ነውና ልባችነን አንጽተን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እንዲሆን የሚያስተምር ነው።
የምኵራብ ዕለተ እሑድ የካቲት ፳፪ ( 22 ) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (March 1/2026) ከደረሱት የስብሐት ነግህ፣ የኪዳን፣ የቅዳሴ፣ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በጥቂቱ፦
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ስታቫንጋር፣ ኖርዌይ