Medhanealem

እንኳን ለጥቅምት መድኃኔ ዓለም በዓል አደረሳችሁ!

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የመድኃኔ ዓለምን የስቅለት በዓል ጥቅምት ፳፯ በድምቀት ታከብራለች፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደሙን ያፈሰሰው ቅዱስ ሥጋውን የቆረሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፣ እርሱም በጥንተ ስቅለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን ነው። መጋቢት መድኃኔ ዓለም ግን በዓቢይ ጾም ወቅት ስለሚውልና በዓቢይ ጾም ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በፍትሐ ነገሥት ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ሰርታልናለች፡፡ በመኾኑም ጥቅምት ፳፯ የስቅለት መታሰቢያ የለውጥ በዓል ነው፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን!

በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት
የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
ኖርዌይ፣ ስታቫንጋር