4.ሥላሴን አመስግኑ

ሥላሴን አመስግኑ (2)

የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ (2)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት

ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ

ምስጋና ይገባል ከጧት እስከ ማታ

አዝ

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ

ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ

ሥላሴ አምባዮ ክብሬም ናቸውና

ሁሌም ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና

አዝ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት

መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት

እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን

በሰማይ በምድር እንጠራሃለን

አዝ

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ

ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ

ሥላሴ አምባዮ ክብሬም ናቸውና

ሁሌም ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና

አዝ