የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምሕረት የንግሥ በዓል በደብረ ገነት መድኃኔዓለም ወኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን በመዝሙር በትምህርተ ወንጌል በማህሌት እና በቅዳሴ ከየካቲት 14 -15, 2018 ዓም (Feb 21-22, 2026) ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤልያስ በተገኙበት በድምቀት ተከበረ።

“ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ” «ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ» መዝ. 88 (89) ፥ 3

የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የየካቲት ኪዳነ ምሕረትን ዓመታዊ ክብረ በዓል በጥቂቱ፦

“ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ”(ጾም የነፍስን ቁስል ትፈውሳለች የሥጋን አላስፈላጊ ፍላጎቶችንም ታስወግዳለች) ቅ.ያሬድ

እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!

ዐቢይ ጾም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀደመው ዘመን ለነበሩት አባቶችና እናቶች ጾም ጠቃሚና አስፈላጊ እንደሆነ በነቢያቱ አድሮ ያስተማረ እርሱ በሥጋ ማርያም ተገልጦ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ፵ (40) መዓልት ፵ (40) ሌሊት የጾመው ታላቅ ጾም ነወ።

እርሱ ጾሞ ፈተናዎችን ድል ነስቶ እናንተም ጾማችሁ ፈተናዎችን ድል ንሡ ሲለን ነው።

ዐቢይ ጾም ከ፯ቱ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የየራሳቸው ስያሜ ያላችው ፰(8) ሳምንታት  ወይም ፶ ፭  (55) ቀናት አሉት።ከእነዚህም ውስጥ ፰(8) ቅዳሜ ፯(7) እሑድ አሉ እነዚህን ከቁጥር ባያስገቡ ፵(40) ቀናት ይሆናል።

የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ይባላል።

ዘወረደ ጌታችን፣ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን፣  የእኛን ሥጋ መዋህዱን  ሰው ኾኖ መገለጡን ይታሰብበታል።

በተጨማሪ ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል፣ ጾመ ሙሴ ተብሎም ይጠራል።

የዘወረደ በዕለተ በእሑድ የካቲት ፰(8) ቀን  ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (February 15/2026) ከከደረሱት የስብሐት ነግህ ፤ የኪዳን ፤ የቅዳሴ ፤ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በትንሹ(በከፊል)፦

Medhanealem

እንኳን ለዘመነ ቅበላ(ዘመነ መርዓዊ ወመርዓት) በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለዘመነ ቅበላ(ዘመነ መርዓዊ ወመርዓት) በሰላም አደረሳችሁ!
ከነነዌ ፋሲካ ሐሙስ ጀምሮ እስከ ዘወረደ ዋይዜማ ቅዳሜ ድረስ ያለው ዘመን ዘመነ ቅበላ (ዘመነ መርዓዊ ወመርዓት) ይባላል።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ክርስቶስን በሙሽራው ፤ እመቤታችን በጫጉላ ቤት ፤
ቤተክርስቲያንን በሙሽሪት መስላ የምታመሰግንባቸው ዕለታት ናቸው።
በዕለተ በእሑድ የካቲት ፩(1) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (February 8/2026) ከከደረሱት የስብሐት ነግህ ፤ የኪዳን ፤ የቅዳሴ ፤ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በትንሹ(በከፊል)፦
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ስታቫንጋር፣ ኖርዌይ

እንኳን ለጾመ ነነዌ በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለጾመ ነነዌ በሰላም አደረሳችሁ!
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የህግ(የቀኖና) አጽዋማት አንዷ ናት ከጥር17 ቀን እስከ የካቲት 21 ቀን ድረስ ባሉት 35 ቀናት ውስጥ ብቻ ትውላለች ከታች ጥር 16 ቀንን ከላይ የካቲት 22 ቀንን አትነካም ዘንድሮ በ2018 ዓ.ም ከጥር 25 እስከ ጥር 27 ቀን ድረስ ትውላች።
‹‹የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ›› ትን.ዮና. ፫÷፭-፮
እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎችን ያዘነላቸው ስለ ኃጢአታቸው አዝነው በመገኘታቸውና ጾም እና ጸሎትን በመያዛቸው ነው። የእግዚአብሔርን ርኅራኄ፣ የነቢዩ የዮናስን የዋህነትና የሕዝቡን የንሥሐ፣ የጾምና የጸሎት ሕይወት እንማርበታለን።
በዕለተ በእሑድ ጥር ፳ ፬(24) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (February 1/2026) ከደረሱት የስብሐት ነግህ ፤ የኪዳን ፤ የቅዳሴ ፤ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በትንሹ(በከፊል)፦
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ስታቫንጋር፣ ኖርዌይ