የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ጥሪ ከነሓሴ 16 እስከ ነሓሴ 18/2017 ዓ.ም (August 22-24/2025)
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰቷን፣ ትንሣኤዋን እና ዕርገቷን ምክንያት በማድረግ በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ
ክብረ በዓል ከነሓሴ 16 እስከ ነሓሴ 18/2017 ዓ.ም(August 22-24/2025) ድረስ ከሊቃውንተ
ቤተ ክርስትያን ፣ ከመምህራነ ወንጌል ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና ከምእምናን ጋር
በትምህርተ ወንጌል ፣ በዝማሬ፣ በሥርዓተ ማህሌት እና በሥርዓተ ቅዳሴ ይከበራል።
በመሆኑም በተጠቀሰው ቀን ተገኘተው የበዓሉ በረከት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በቅድስት ኪዳነ ምህረት
ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን
አድራሻ :- Skippergata 67, 4327 Sandnes