ሁሉም መዝሙራት

ለተክለሃይማኖት ጻድቅ

ለተክለ ሐይማኖት ድቅ

ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነበዝሃ ሕማሙ /2/

ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ/4/

እምነ አድባራት ኩሎን ዘተለአለት በስሙ /2/

ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/

እስመ በዉስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ስጋሁ ወአፅሙ /2/

ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ /4/

ኢየሱስ ክርስቶስ እንተ ቀደሳ በደሙ /2/

ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ /4/

ንሴብሆ ለሥላሴ

ንሴብሆ ለሥላሴ

ንሴብሆ ለሥላሴ /4/

ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ /2/

 

የእኛ አማላጅ እናታችን /4/

ነይ ነይ ወደኛ እመቤታችን ፈጥነሽ ተገኚ መሃከላችን(2)

ና ወደእኛ ሚካኤል /4/

መልአከ ምክሩ ለልዑል ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል(2)

ና ወደእኛ ገብርኤል /2/

ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል በክንፍህ ጥላ እንጠለል(2)

 

ንሴብሆ ለሥላሴ /4/

ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ /2/

 

ና ወደ እኛ ዑራኤል /4/

እንደ ቅዱስ ዕዝራ ሱቱኤልጥበብን ስጠን ማስተዋል(2)

ና ወደእኛ በፈረስ /4/

የልዳው ፀሐይ ጊዮርጊስ ገድልህን ሰምተን እንፈወስ(2)

ና ወደእኛ ተክለሃይማኖት /4/

ይጠብቀን የአንተ ጸሎት ጸንተን እንድንቆም በሃይማኖት /2/

 

ንሴብሆ ለሥላሴ /4/

ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ /2/