እንኳን ለዘመነ አስተርእዮ በሰላም አደረሳችሁ!
እንኳን ለዘመነ አስተርእዮ በሰላም አደረሳችሁ!
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ከጥር ፲፩(11) እስከ ድኅራረ ጾም ቅዳሜ ደረስ ያለው ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ይባላል።( ዘመነ አስተርእዮ ሲበዛ ፶፫(53) ቀን ይሆናል ከጥር ፲፩ (11) እስከ መጋቢት ፫(3) ድረስ ማለት ነው ፤ ሲያጥር ፲፱(19) ቀን ይሆናል ከጥር ፲፩(11) እስከ ጥር ፳፱(29) ቀን ድረስ ማለት ነው።ከእነዚህ ቀናት መካከል አይወጣም።
በዘንድሮው ዘመን ደግሞ ከጥር ፲፩(11) እስከ የካቲት ፯ (7) ቀን ድረስ ያለው ዘመነ አስተርእዮ (የመገለጥ ዘመን) ይባላል። በውስጡ ስምዖን ፤ ነነዌ እና መርዓዌ(ቀበላ) የሚባሉ ንኡሣን ክፍሎች አሉት።
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ የኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በዕለተ በእሑድ ጥር ፲ ፯ (17) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (January 25/2026) ከደረሱት የስብሐት ነግህ ፤ የኪዳን ፤ የቅዳሴ ፤ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በትንሹ(በከፊል)፦

