ኦ ፍጡነ ረድኤት

ፍጡነ ረድኤት

ኦ ፍጡነ ረድኤት /2/

የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሰማዕት

 

ሰላም ላንተ ይሁን _ ፍጡነ ረድኤት

የልዳዉ ፀሐይ _ ፍጡነ ረድኤት

በጨካኝ ንጉሥ ፊት ቆምክ አደባባይ

ታማኝ አገልጋይ ነህ _ ፍጡነ ረድኤት

ስቃይ ያልበገረህ _ ፍጡነ ረድኤት

አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሰህ

አዝ

የፈጣሪዉን ስም _ ፍጡነ ረድኤት

ስለመሰከረ _ ፍጡነ ረድኤት

ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ

የስቃይ መሳሪያ _ ፍጡነ ረድኤት

ያላዘናጋህ _ ፍጡነ ረድኤት

መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ

አዝ

ለእምነቱ ተጋዳይ _ ፍጡነ ረድኤት

ታማኝ ወታደር _ ፍጡነ ረድኤት

ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር

ስቃይ ሲያደርሱብህ _ ፍጡነ ረድኤት

በመታገስህ _ ፍጡነ ረድኤት

ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ

አዝ

ለሰማዉ ይደንቃል _ ፍጡነ ረድኤት

የአንተ ሰማዕትነት _ ፍጡነ ረድኤት

ምሳሌ ይሆናል ለሁሉም ፍጥረት

ገድልከ ይናገራል _ ፍጡነ ረድኤት

ክብር እንደተሰጠህ _ ፍጡነ ረድኤት

ጊዜ የማይሽረዉ ምግባር ሃይማኖት

አዝ