የደብሩ አስተዳዳሪ የ2013 ዓ.ም. የአዲስ አመት መልእክት አስተላለፉ

በስመ አብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
አንትሰ አንተ ክመ ። ወዓመቲከኒ ዘኢይኀልቅ:: “አንተ ግን ያው አንተ ነህ ፤ ዓመቶችህም  ከቶ አያልቁም” መዝ ፦101(102) ፥ 27

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ፳፻፲፪ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ፳፻፲፫ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ ! አዲሱን ዓመት የንሥሓ ፣የፍሥሓ የበረከትና የምህረት ፣ የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን ! ከተዋሕዶ ማማ ፣ ከመስቅል ዓላማ ፣ከወንጌል ከተማ ሳያናውጽ በቤቱ በሃይማኖት በምግባር አጽንቶ ያኑረን!! ስለ ሀገራችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ህዝበ እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበት የምናይበት ዘመን ያድርግልን::ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር አይለየን አሜን ።የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ አድሮ ፀንቶ ይኑር::