3.ለገታዬ ለእግዚአብሔር

ለገታዬ ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ምን እከፍለዋለሁ (2)

ምስጋና ነዉ እንጂ (2) ሌላ መን እላለሁ(4)

 

ለእመቤቴ ለድንግል ማርያም ስላማለደችኝ ምን እከፍላታለሁ

ላመስግናት እንጂ(2) ሌላ መን እላለሁ(4)

የደብሩ አስተዳዳሪ የ2013 ዓ.ም. የአዲስ አመት መልእክት አስተላለፉ

በስመ አብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
አንትሰ አንተ ክመ ። ወዓመቲከኒ ዘኢይኀልቅ:: “አንተ ግን ያው አንተ ነህ ፤ ዓመቶችህም  ከቶ አያልቁም” መዝ ፦101(102) ፥ 27

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ፳፻፲፪ ወደ ዘመነ ማቴዎስ ፳፻፲፫ በሰላም አሸጋገረን አሸጋገራችሁ ! አዲሱን ዓመት የንሥሓ ፣የፍሥሓ የበረከትና የምህረት ፣ የሰላምና የፍቅር ዓመት ያድርግልን ! ከተዋሕዶ ማማ ፣ ከመስቅል ዓላማ ፣ከወንጌል ከተማ ሳያናውጽ በቤቱ በሃይማኖት በምግባር አጽንቶ ያኑረን!! ስለ ሀገራችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ህዝበ እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበት የምናይበት ዘመን ያድርግልን::ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር አይለየን አሜን ።የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ አድሮ ፀንቶ ይኑር::

 

የደብሩ ድረገጽ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ ቀረበ

ለብዙ አመታት በስራ ላይ ውሎ የነበረው የስታቫንገር የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ድረገጽ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ የቀረበ ሲሆን በድረገጹ መሰረታዊ መረጃዎች፤ወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም ከቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ እና ከደብሩ እንቅስቃሴዎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ መረጃዎች ተካተውበታል። ድረገጹ በአማርኛ እንዲሁም በኖርዌጅያን ቋንቋዎች ተዘጅቶ ቀርቧል።

በቀጣይም ከደብሩ የአባላት መከታተያ እና በኮምፒውተር የተደገፉ አሰራሮች አጋዥ ማስተግበሪያ (ፖርታል) ጋር ተያያዥ እንዲሆን እንደሚደረግ ታውቋል።