ስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
    • ታሪክ
    • አገልጋዮች
  • አገልግሎቶች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • የመድኃኔአለም መዝሙራት
    • የእመቤታችን መዝሙራት
    • የመላእክት መዝሙራት
    • ሁሉም መዝሙራት
  • ይለግሱ
  • የፎቶ ማኅደር
  • ያግኙን
  • Menu Menu

እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

“እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፤ ወአምላክነሂ ኢያረምም፤ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡” እግዚአብሐር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳቱ በፊቱ ይቃጠላል፡፡ መዝ.፵፱፥፪-፫
እንኳን ለዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት (ደብረ ዘይት) በሰላም አደረሳችሁ!
“ደብረ ዘይት” ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ በደብረ ዘይት ላይ የዓለም ፍጻሜ ምን እንደሚመስል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል፡፡ “እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክትስ ምንድን ነው“? አሉት /ማቴ ፳፬፥፫/ የዓለም ኅልፈት መቼ እንደሆነና ምልክቱ ምን እንደሆነ ለተጠየቀው ጥያቄ ጌታችን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የዓለም ኅልፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ የምትታወቅ እንጂ ቀኒቱ ለሰው ልጅ ተለይታ የማትታወቅ መሆኗን ተናግሯል፡፡ በዓለ ደብረ ዘይት ቤተክርስቲያናችን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፣ እነዚኽም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ጌና፣ ግዝረት፣ ልደተ ስምዖን፣ ቃና ዘገሊላ፣ ደብረ ዘይትና መስቀል ናቸው፡፡
የደብረ ዘይት ዕለተ እሑድ መጋቢት ፮ ( 6 ) ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ (2018) ዓ. ም (March 15/2026) ከደረሱት የስብሐት ነግህ፣ የኪዳን፣ የቅዳሴ፣ የስብከተ ወንጌልና የዝማሬ አግልግሎት መካከል በጥቂቱ፦
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/photo_2026-03-15_16-12-40.png 497 365 Nigussie Girma https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/eotc-stavanger-logo2.png Nigussie Girma2026-03-15 17:08:492026-03-15 17:10:58እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Search Search

Recent Posts

  • “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።” መዝ ፵፮፥፭
  • የእሑድ ግንቦት ፪ ቀን  ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (May 10/2026)
  • እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!!!
  • እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ (ለመጋቢት መድኃኔ ዓለም) ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሆሣዕና አደረሳችሁ!
  • እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ!

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • November 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • November 2024
  • June 2021
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • August 2014
  • August 2012
© የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ | Administration | Email | Members Portal
Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳች... Link to: እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ)...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top