እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ አባታችን ናቸው። በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያም ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች። የጻድቁ በረከት አይለየን!
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት
የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
ስታቫንጋር ኖርዌይ
እሑድ ነሐሴ ፳፬ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (August 30/2026)

