ስታቫንገር ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
    • ታሪክ
    • አገልጋዮች
  • አገልግሎቶች
  • ሰንበት ት/ቤት
    • የመድኃኔአለም መዝሙራት
    • የእመቤታችን መዝሙራት
    • የመላእክት መዝሙራት
    • ሁሉም መዝሙራት
  • ይለግሱ
  • የፎቶ ማኅደር
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የ፳፻፲፰ በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ ክርስትያንሳንድ

“አሜሃ መጽአ ኢየሱስ እምገሊላ ውስተ ዮርዳኖስ ኀበ ዮሐንስ ከመ ይጠመቅ እምኔሁ” ማቴ 3:13 (“ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ”)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስና ወደ ዮሐንስ የሄደበትን መነሻ አድርጋ በየዓመቱ ጥር ፲ እና  ፲፩ ታቦታተ ኅጉን ከመንበረ ክብራቸው (ከቤተ ክርስቲያን) አንስታ ወደ ወንዝ በመሄድ የጥምቀትን በዓል በደማቅ ታከብራለች።በመሆኑም በውጭ ሀገር የሚኖሩ ልጆቿም ይህንኑ መሠረት አድርገው በየአሉበት በዓሉን ያከብራሉ።
በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ
የጥምቀት በዓል በኖርዌይ ሀገር በጋራ ማክበር ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረው በኦስሎ ከተማ በጥር ወር በ 2004 ዓ.ም ነበር። በዓሉ ለኹለተኛ ጊዜ በስታቫንጋር  በ 2005 ዓ.ም፣ ለሦስተኛ ጊዜ በበርገን በ 2006 ዓ.ም፣ ለአራተኛ ጊዜ እንደገና በድጋሜ በስታቫንጋር በ 2007 ዓ.ም፣ ለአምስተኛ ጊዜ በክርስቲያንሳንድ በ 2008 ዓ.ም፣ ለስድስተኛ ጊዜ በትሮንዳሔም በ 2009 ዓ.ም፤ ለሰባተኛ ጊዜ በስታቫንጋር በ 2010 ዓ.ም፤ ለስምንተኛ ጊዜ በበርገን በ 2011 ዓ.ም፤ ለዘጠነኛ ጊዜ በክርስቲያንሰንድ በ 2012 ዓ.ም፤ በ 2013 ዓ.ም እና በ 2014 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በዓሉ ሳይከበር ቀርቷል።
ለአሥረኛ ጊዜ በኦስሎ በ 2015 ዓ.ም፤ ለአሥራ አንደኛ ጊዜ በስታቫንጋር በ 2016 ዓ.ም፤ ለአሥራ ሁለተኛ ጊዜ በበርገን በ  2017 ዓ.ም፤ ለአሥራ ሦስተኛ ጊዜ ዘንድሮ በክርስቲያንሳንድ በ 2018 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል።  በእነዚህ በተለያዩ ዓመታት በጳጳሳት፣ በመነኮሳት፣ በቀሳውስት፣ በዲያቆናት እና በኖርዌይ የሚኖሩ ምዕመናንና ምዕመናት ባሉበት ተከብሯል።
የጥምቀት በዓል በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩ ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው። ይህ ሃይማኖታዊ በዓል የአንድነት የሦስትነት ምሥጢር የተገለጠበት፣ የአምላክ ትሕትና ለዓለም የታወቀበት፣ የዕዳ ደብዳቤያችን የተደመሰሰበት፣ የሰው ልጆች ልዕልና የተረጋገጠበት፣ የድኅነት በር የተከፈተበት ታላቅ በዓል ነው። ጥንታዊት ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን አምላኳ ክርስቶስ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክትን ትቶ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ቁሞ ፈጣሪ ሲሆን በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ መጠመቁን በየዓመቱ ታስባለች።
መልካም በዓል!
ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘወለደነ ዳግመ በጥምቀቱ !!!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/photo_2026-01-18_20-22-15-705x529-1.jpg 468 395 Nigussie Girma https://eotc-stavanger.no/a/wp-content/uploads/eotc-stavanger-logo2.png Nigussie Girma2026-01-18 19:44:032026-01-25 14:15:50የ፳፻፲፰ በዓለ ጥምቀት በሀገረ ኖርዌይ ክርስትያንሳንድ
Search Search

Recent Posts

  • የእሑድ ግንቦት ፪ ቀን  ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (May 10/2026)
  • እንኳን ለስቅለት በዓል አደረሳችሁ!!!
  • እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ (ለመጋቢት መድኃኔ ዓለም) ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሆሣዕና አደረሳችሁ!
  • እንኳን ለዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት (ኒቆዲሞስ) በሰላም አደረሳችሁ!
  • እንኳን ለደብረ ዘይት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Archives

  • May 2026
  • April 2026
  • March 2026
  • February 2026
  • January 2026
  • November 2025
  • September 2025
  • July 2025
  • November 2024
  • June 2021
  • October 2020
  • September 2020
  • August 2020
  • July 2020
  • August 2014
  • August 2012
© የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን - ስታቫንገር ኖርዌይ | Administration | Email | Members Portal
Website by atbiya.com
  • Link to Facebook
Link to: እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለዘመነ አስተርእዮ በሰላም አደረሳችሁ! Link to: እንኳን ለዘመነ አስተርእዮ በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን ለዘመነ አስተርእዮ በሰላም አደረሳች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top