“ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።” መዝ ፵፮፥፭
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን…በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን…አግዓዞ ለአዳም
ሰላም… እምይእዜሰ
ኮነ…ፍሥሓ ወሰላም
“ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ። ወእግዚእነ በቃለ ቀርን። ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።” መዝ ፵፮፥፭
ዕርገተ ክርስቶስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ዕርገት የክርስቶስ የማዳን ሥራ ምድራዊ ክፍል ፍጻሜ ነው። በሥጋ ተገልጦ፣ አስተምሮ፣ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ተነሥቶ ካሳየን በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ፣ ወደ አባቱ መመለሱን ያመለክታል። ጌታችን ያረገው ሥጋ ለባሽ ሆኖ ነው፤ ይህም ሥጋችን በሰማያት ቦታ እንዳለውና እንደሚከብር ያረጋግጥልናል። አምላካችን እግዚአብሔር ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ አሜን።
በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በኖርዲክና ግሪክ ሀገረ ስብከት
የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን
ስታቫንጋር ኖርዌይ
እሑድ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም (May 24/2026)

